Sunday, January 11, 2026

አዲስ አመት

አዲስ አመት

መስከረም ባይሆንም፣ አደይ ባይፈንዳ፣ 

አለም ተነሳ፣ አዲስ ቀን ሊነዳ። 

የጃንዋሪ ወር፣ የዘመን መለወጫ፣ 

ለሰው ልጅ በሙሉ፣ የተስፋ መውጫ።

ቁጥሩ ተቀየረ፣ ታሪክ ተለወጠ፣ 

ለህዝብ ሁሉ፣ ብርሃን ተሰጠ።

ርችት ሲተኮስ፣ ሰማዩ ሲደምቅ፣

ሰው ሰውን ሲጋብዝ፣  ሲጠይቅ፣

የሰው ወርቅ አያደምቅ፣

የኔ ሃሳብ እንቁጣጣሽ ላይ ነው፣  እና መረቅ።