Tuesday, January 3, 2017

ሁሉንተናዊ ፡ እብደት

    የፍጥረት ምክንያታዊነት የሚመነጨው ከፍጥረት ድርጊት ነው ካለ ድርጊት ምክንያት ሊኖር ኣይችልምና። ታድያ በፍጥረት ውስጥ እንደ ሰው ያለ ድርጊት ፈፃሚ ድርጊት ሲፈፅም የድርጊቱ ቋሚ ምክንያት የኣድራጊው ሌላ ድርጊት መሆን የለብትም ምክንያቱም ላዛ ምክንያት ተባይ ድርጊት ሌላ ምክንይት ሊኖረው ይገባልና። ለምሳሌ አንድ ሰው አያለቀሰ ኣገኘነው እንበል። ለምንድን ነው የምታለቅሰው ብንለው ስላዘንኩ ነው ብሎ መለሰልን እንበል። ማዘኑ የራሱ ድርጊት ነው። ማለትም ማዝኑን የፍፀመው  እራሱ ነው። ስለዚህ ቀጥለን ለምን አዘንክ ብለን ጠየቅነው። ስላመመኝ ብሎ መለሰልን። አሁንም መታመሙን የፈፀመው ወይም የተገበረው እሱ ነው።  ስለዚህ ቀጥለን ለምን አመመህ ብለን ጠየቅነውና መስተርድ ጭስ በአውሮፒላን ሰለተጣለብኝ ነው አለን። አሁን መጠየቅ ማቆም እንችላለን ምክንያቱም ይሄን ድርጊት እሱ ኣልፈፀመውምና። ላልፈፀመው ድርጊት ምክንያት ሊሰጥ ኣይገባም። ስለዚህ የማልቀሱ ቋሚ ምክንያት (ምክንያት የማያስፈልገው ምክንያት) ከሰውየው ድርጊቶች ውጪ ነው። ይሄ ለምንኛውም አድራጊና ድርጊት እውነት ነው።

     ፍጥረት ውስጥ ብዙ አድራጊዎች ቢኖሩም ፍጥረት በአንድ ላይ እንደ አንድ አድራጊ ሊውሰድ ይችላል።
ታድያ ፍጥረት (የፍጥረት አባል) ድርጊት ሲፍፅም ቋሚ ምክንያቱ ፍጥረት ውስጥ ሊሆን አይችልም። በተጨማሪም ከፍጥረት ውጪ ከፈጣሪ በስተቀር የለም። ስለዚህ ካላፈጣሪ የፍጥረት ድርጊቶች ሁሉ ያለቋሚ ምክንያት ናቸው። ይሄንን ሁኔታ ሁሉንተናዊ  እብደት ልንለው እንችላለን።

     ሁለንተናዊ እብደት ለኛ ምን ትርጉም አለው? ለኛ የሚነግረን የህይወታችን ትርጉም  ካለፈጣሪ በምክንያት ላይ የተመስረተ እንዳልሆነ ነዉ። ምክንያታዊ ኑሮ የሚቻለዉ በፈጣሪ እምነት ብቻ ነዉ። በፈጣሪ ካላመንን መኖር እነችላለን ግን ኑሮአችን ምክንያታዊ ሳይሆን እንደዛር  ምክንያት ፈጣሪ እና ተግባሪ ነው።